|

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆኑ. Ethiogermany sends Congratulation Message to him.

የኢህአዴግ ምክርቤት ጉባኤ ተጠናቆአል። ምክርቤቱ ሃይለማርያምና ደመቀን ዋና እና ምክትል አድርጎ መርጦአል። በዚህ ምርጫ አነጋጋሪ የሆነው፣ ከምርጫው በፊት፣ “ታጋይ የነበረ ለምርጫ አይቀርብም” በሚል ማሳሰቢያ ከበረሃ የገቡ ታጋዮች ሁሉ ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸው አንዱ ነበር። በጥቆማው ወቅት ከህወሃት እጩ ሆኖ ለውድድር የቀረበ አለመኖሩ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። ሶስት ሰዎች ተጠቆሙና ሁለቱ ተመረጡ።
ሶስተኛው ተወዳዳሪ ሶፊያን አህመድ ነበር። ሶፊያን አህመድን የጠቆመችው አዜብ ነበረች። እንዲመረጥላትም አስቸግራ ነበር። ችላ ሲሏት ተወችው። በረከት ስምኦን መግለጫ ሲሰጥ የሶፊያን አህመድን ስም ለምን መጥራት እንዳልፈለገ ግን አልገባኝም።“ሶስተኛውን ተወዳዳሪ ስም መጥቀስ አያስፈልግም” ሲል ዘለለው።መቼም እነዚህ ሰዎች ምስጢር ሲወዱ ጉድ ነው። እነሱ ቢደብቁት እኛ ምን ስራ አለን? እንገሸልጠዋለን። የእኛ የጋዜጠኞች ጆሮ እንኳን ሰምቶ፣ ሳይሰማም ቀዥቃዣ ነው። የሆነው ሆኖ፣ “ከበረሃ የመጡት ታጋይ ባለስልጣናት ከእንግዲህ ወደስልጣን አይመለሱም” ተብሎአል። እያማከሩ ቆይተው በዚያው ወደ ጡረታ ይሸኛሉ። ይህ ዜና መቼም “እፎይ” አሰኝቶኛል።

የእኛ የጋዜጠኞች ጆሮ እንኳን ሰምቶ፣ ሳይሰማም ቀዥቃዣ ነው። የሆነው ሆኖ፣ “ከበረሃ የመጡት ታጋይ ባለስልጣናት ከእንግዲህ ወደስልጣን አይመለሱም” ተብሎአል። እያማከሩ ቆይተው በዚያው ወደ ጡረታ ይሸኛሉ። ይህ ዜና መቼም “እፎይ” አሰኝቶኛል። እንዲህ ማሰብ መጀመራቸው ራሱ አንድ ፀጋ ነው። ህይወት ከንቱ መሆኗን ከመለስ ህይወት ተምረዋል። እንዲህ እንደጀመሩት፣ በነካ እጃቸው እስረኛ ቢፈቱ፣ በአካባቢያችን ላይም ሰላም እንዲሰፍን አንዳንድ እርምጃ ቢወስዱ፣ ነፍሳቸው ገነት ትገባለች።ከትናንቱ ምርጫ ጋር በተያያዘ መልከ ብዙ አስተያየቶች እየጎረፉ ነው። የህወሃት ሰዎች አካባቢ መደናገጥ ይታያል። በአንፃሩ በተቃዋሚዎች በኩል ግራ መጋባት ሰፍኖአል። “የምር ህወሃት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አካባቢ ተሰናበተ?” ገና ግልፅ አይደለም።

ስዩም ጤና የለውም። በጣም ታሞአል። ለነገሩ ማን ያልታመመ አለ? ስኳሩ፣ ደምግፊቱ፣ ሪህ፣ እንትን፣ ስምአይጠሬ፣ ኩላሊት፣ ጉበት፣ ልብ፣ ሳምባ፣ ካንሰር፣ ወፈፌነት፣ ምኑ ቅጡ… የኢህአዴግ አመራር ውስጥ የሚሰማው የበሽታ አይነት ሲመዘን፣ ሁሉንም የበሽታ ተዋፅኦ የጠበቀ ይመስላል። መቀለዴ አይደለም። በበሽታ ምን ይቀለዳል? 40 አመት ያለፈው አበሻ አንድ በሽታ አያጣውም። እኔ ራሴ ቮድካ ስቀምስ ልቤን ይከዳኝ ጀምሮአል።የሆነው ሆኖ “የህወሃት ዘመን አበቃለት” የሚሉ ወሬዎች አሉ። መቸኮል እንኳ አያስፈልግም። “ህወሃቶች ከጀርባ ሆነው አገር መምራታቸው አይቀርም” የሚሉትንም ማድመጥ ያስፈልጋል። ሁኔታዎች የተደበላለቁ ቢመስሉም በአንድ ነገር ግን መግባባት ይቻላል። የህወሃት ሰዎች አማራጭ ስላጡ ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስቱ ተገፍትረው ወጥተዋል። ተስፋ የሚያደርጉት ደህንነት እና መከላከያን በመያዛቸው ነው። ይሄ ግን ከንግዲህ አያስኬድም። ሃይለማርያምን እንዲዋሽ ማስገደድ ያስቸግራቸዋል። ሰውየው ጥብቅ ሃይማኖተኛ እንደመሆኑ፣ መግደልና መዋሸት ውስጥ ለመግባት ይቸገራል። ደህንነቱ ሰው ቢገድል የሚጠየቀው ሃይለማርያም እንደመሆኑ፣ ስራውን መልቀቅ ወይም ስለተፈፀመው ድርጊት ማብራራት ይኖርበታል። በመሆኑም ህወሃት ደህንነቱን ስለያዘ ሃገሪቱን ሙሉ በሙሉ ያሽከረክራል ማለት ላይሆን ይችላል። እና መቸኮል አይገባም። ነገም ሌላ ሰንበት አለ።የሃይለማርያም ሹመት በፓርላማ ከፀደቀ በሁዋላ፣ የራሱን አዲስ ካቢኔ እንደሚመሰርት ይጠበቃል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኦህዴድ የታሰበ ቢሆንም፣ የህወሃት ሰዎች “ብርሃነ ገብረክርስቶስ መሆን አለበት” ሲሉ ቸክለዋል። ወርሃ ጥቅምት ላይ የሚሆነውን እናያለን። በአዲሱ ካቢኔ ደህንነት እና መከላከያ ያለምንም ጥያቄ በህወሃት እጅ የሚቆዩ ሲሆን፣ የሌሎች የሚኒስትር መስሪያ ቤት ስልጣናት እጣ ፈንታ ገና አልታወቀም።አዲስ አበቤ መቸም ቀልድ ይወዳል።ማምሻውን ቢራ ላይ ቀልዶች ፈልተው ነበር አሉ። ከተፈጠሩት ቀልዶች አንዱ፣ “የህወሃት ሰዎች መለስን ከላይ አስቀምጠናል በሚል እምነት፣ ገንዘብ ሲያሳድዱ ተተኪ ባለማዘጋጀታቸው ስልጣኑ ከእጃቸው አመለጠ።” የሚለው ፉገራ አንዱ ነው።የህወሃት ሰዎች በበኩላቸው፣ “የዚህ ሁሉ ተንኮል ጠንሳሽ በረከት ስምኦን ነው” በሚል ጥርስ ነክሰውበታል። ይሄ ሰውዬ ምን ይሻለዋል? ጠላቱ በዛ። ጀግና ነው ግን። ታንክ የመሰለ ግንባሩን ደቅኖ ሁሉን ተቋቁሞ እዚህ ደርሶአል። በረከት – የስምኦን ልጅ።መለስና ጳጳሱ የተቃጠሩ ይመስል ተከታትለው ሄደው፣ ባልተጠበቀ ፍጥነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የኢህአዴግ ከፍተኛ ስልጣናት ከህወሃት እጅ መሹለካቸውን፣ “የእግዚአብሄር ተአምር” በሚል የሚገልፁም ተደምጠዋል። የፈረደበት እግዚአብሄር ያለፍላጎቱና ያለግብሩ ፖለቲካ ውስጥ እየተነከረ መከራውን ያያል። እግዜር ይርዳው!

The first and most important thing HE Hailemariam should do is to abolish the failed approach of seeing Ethiopians primarily in their ethnic light. This means, abolish extra flags, separate regime flag from the plain Ethiopian flag, and remove the impractical ethnicity section from identity cards. We are all humans first, and simply because of this, we should all be treated equal. Ethiopians shouldn’t need labels, flags, permissions or affirmation to exercise their respective cultures, languages or preferences. EPRDF cannot give or deny god given rights of the Ethiopian people, nor can any of the preceding regimes. Only the rule of law is required.
2. Reform institutions: HE Hailemariam needs to start the long and hard process of cleansing the major civic institutions from political influence and to put them back into the people’s hands. This means the justice system security, military, and even religious ones. Especially the recent laws specifically designed to target people who speak up against the regime need to be abolished.
3. The Media space should be opened back up.
This is important. With a reformed justice system, then anyone that violates the rules will be held accountable, but only after the media institution as well as justice institution is put in the hands of the Ethiopian people and not the regime.
4. The political space needs to be opened up so that both exiled and internal groups can participate in the process. Again, with rule of law in place, there would be no fear of persecution. Instead of the regime streaming 24/7 propaganda about the evils of opposition, let the people decide. This is a way to measure the confidence of the party in power. If there’s to be real democracy, open up the political space.
5. Release political prisoners. Release political prisoners. Release political prisoners.

You see, the government works for the people, not the other way around. Frankly speaking, everyone knows what the deal has been for the past 21 years. Let this chance not be squandered. If EPRDF is confident, let the actions show the reality, not the propaganda campaigns. When people feel like they have rights, Ethiopia will develop further. As to Eritrea, either return Badme or come up with another solution. As to Somalia, stop squandering our military and economic resources to do the bidding of the US. The Government needs to be transparent in exactly what the cost of our incursions are into Somalia is (Meles refused). Unless the regime manages to gain credibility by working for it, no one will ever trust anything that comes out of its channels, such as charges of terrorism, islamic extrimism, or anything else. Simply, the regime needs to earn the trust of the Ethiopian people. Stop the lies.

Short URL: http://www.ethiogermany.de/?p=5212

Posted by on Sep 18 2012. Filed under Headlines. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. You can leave a response or trackback to this entry

Leave a Reply

English       በአማርኛ ይፃፉ    Ge'ez: [download] [help] [keybord]

May 2016
S M T W T F S
« Apr    
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293031