ሰብረውንም ከሆነ ነገ ይታያል ! -Tamagne Beyene

ትናን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት በመስቀል አደባባይ ያደረገው ንግግር፣ከሰማኒያ አራት ዓመት በፊት ቤኒቶ ሙሶሎኒ በፒያሳ ሮማ አደባባይ ፣የኢታሊያ ጦር አዲስ አበባን የቆጣጠረ እለት ካደረገው የድንፋታ ንግግር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው። ልክ እንደጣልያን ፋሽስቶች ሁሉ፣ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄረተኞች፣ በእብሪትና ማን አለብኝነት እያስተላለፉት ያለው አደገኛ መልእክት ቀስ በቀስ እያለ ወደሚፈራው የእልቂት እያቃረበን ነው። በፖለቲካ ቋንቋ “አከርካሪያቸውን ሰበርን” የሚለው አነጋገር ትንኮሳ አዘል ብቻ ሳይሆን፣ የጦርነት አዋጅ ጭምርም ነው። ይህ አይነቱ መረን የለቀቀ ንግግር በአንድ ሃገር በሚኖሩ ማህበረሰቦች መሃል አይደለም፣ የሁለት የጎረቤት ሀገር ህዝቦች መቃቃርን የሚያጎለብት ነው። ሃይቅ ሳይኖር ሰው ሰራሽ ኩሬ (artificial lake )ስርቶ ኢሬቻን መሃል ከተማ ላይ ማክበሩ ከፖለቲካዊ ድራማነት ያለፈ ሌላ አላማ እንደሌለው ቢታወቅም፣ “የአከርካሪያቸውን ሰብረን” ንግግር የአስተያየቱን ትክክለኝነት አረጋግጦአል። ጣልያን የአርባ አመት ቂሙን ለመወጣት ተዘጋጅቶ ያልተሳካለትን ለሃገር ነጻነት የመቆም ነፍጠኝነትን፣ የኦሮሞ ብሄረተኝነት የአርባ ዓመት የሃሰት ትርክት በወለደው የባለ ግዜነት እብሪት እንደማይሰበር ከታሪክ መማር ጠቃሚ ነው።

Recommended For You

About the Author: admin