ቅሬታ ወይም አስተያየት !

ትላትና ፍራንክፈርት የኢትዩጵያን ባንዲራ ይዛችሁ አትገቡም ብላችሁ አጉላልታችሁናል አሸማቃችሁናል ዲሞክራት በሆነች ሀገር ሰው እንዴት መብቱን ይነጠቃል? አብዛኞቹም ስደት የመረጡት ጭቆና ሰልችቶአቸው ነው ስለዚህ ብታርፉ ጥሩ ነው አልደረስንባችሁም አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው ይህችን ባንዲራ ሰተውናል በደም የተነከረ ማንነታችን ነው የፈለጋችሁትን ውሰዱ ግን በባንዲራ እንዳትመጡብን ሌላው አስተናጋጆቹ ሁሉ የኦነግን ባንዲራ ለብሰው ዱላ ባልተናነሰ መልኩ ሲግላምጡን ቆዩ በጣም የገረመኝ ነገር ካሜራ ማኑ እኛን ባንዲራችንን መቅረፅ ተፀየፈ በኃላም እስቴዲየሙ ዉስጥ ጩኽት በረከተ የተወሰኑ ሰዎች ተናግረውት ተስተካክሎአል እኔም ኢትዮጵያን ላያት ሄጄ ኢትዮጵያን ሳላያት ተመለስኩ we need freedom. _Lamrot Melise


ትናንትና በፍራክፈርት በተደርገው የዶር አቢይ ኣቀባበል ስነስርአት ላይ ብዙ አቤቱታ አለን የሚሉ ሰዎች አየበዙ ነው። ቅሬታችሁን ወይም አስተያየታችሁን ላኩልን፥ ለሚመለከተዉ ባለስልጣን አናደርሳለን።

Recommended For You

About the Author: admin

2 Comments

 1. ለምን ? ማን ይጠየቅ?
  በዶ/ር አብይ የፍራንክፎርት ጉብኝት የኦነግ አርማ በመግቢያው በር ላይ ተሰቅሎ የሚታየው ነው
  እሄን ያለያዘ እንዳይገባ በማለት ለጠባቂዎች ትዛዝ በመሰጠቱ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይዘን ለመግባት የነበረው መከራና ውዝግብ እጅግ የሚያናድድና
  ለተቃውሞ የሚጋብዝ ነበር
  ሆኖም በአዘጋጆቹ ውስጥ ያልተደመሩ መኖራቸውንና ላኖሩ እንደሚችሉ የተረዳው ህዝብ ሰንደቅ ዓላማውን እየተወ ፣ግማሾቻችን ከልብሳች ውስጥ በመልበስ የፍቅር መሪያችንን እንኳን ደህና መጣህ ለማለት ወደ ውስጥ አመራን ውስጥ ከገባሁ በኋላ እንደተረዳሁት በአዘጋጆቹም ይሁን በቆንሲላው ውስጥ ያሉ የቀን ጅቦች ተላላኪዋች ማስተላለፍ የፈለጉት ህብረተሰቡ በለውጡ ላይ እምነት እንዳይኖረውና በየ ኤምባሲው ውስጥ እንደቀደመው የአንድ ዘር የበላይነት እንዳለ በማሳየት ዶ/ር አብይን ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት ነበር
  ሆኖም እስከ መጨረሻው ህዝቡ በጽናት በሚከፈቱት ባህላዊ ሙዚቃዋች ኢትዮጵያዊነትንና እራሱን ከፍ አድርጎ
  መቆዘሙን ቀጥሏል
  ዶ/ር አብይ ወደ መድረኩ ሲወጡና በሜዳው ላይ ባለው እስክሪን ብቅ ሲሉ እና ንግግፘቸውን ሲጀምሩ ጨዋቴው ተለወጠ ኢትዮጵያዊነት ከፍ ከፍ አለ
  እውነት ነው ድንቅ መሪ፣ ደፋር ፣ትሁት፣ቁጡ፣ብልህ፣ፍቅር ውስጡ ያለ፣
  ፍቅርን መቀበል የሚችል የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ

 2. Hanisha Solomon
  1. November um 22:47 ·
  በኔ ላይ የተሰራው ተንኮል ብቻ ሳይሆን ከታላቋ #ብርታኒያ በሄዱትም ላይ ተደገመ….
  በፍራንክፈርት ከተማ ዶር #አብይን ለመቀበልና ላመጡት ለውጥ ምስጋና ለማቅረብ በተደረገው ዝግጅት ላይ #በጀርመንየኢትዮጲያ ኢምባሲ ዝግጅቱ ያልተሳካ እንዲሆን በተለያየ ዘዴ #ህዝብ እንዳይወጣና ደስታውን እንዳይገልጽ ያደረጉትን ሴራ በብሪታኒያ ነዋሪ የሆነው የፎቶ ጋዜጠኛ አቶ #አለባቸውደሳለኝ በዶር #አብይና በታዳሚው እንዲሁም በአለም ዙሪያ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ዝግጅቱን ይከታተል በነበረው #ህዝብ ፊት የኢምባሲውን የወያኔ ቅጥረኞችን የሰሩትን ሴራ አጋለጠ…..
  ውሸታምና ሌባ ምን ጊዜም ክብር አይገባውም!
  ዶር #አብይ ሆይ በዚህ አጋጣሚ እባክዎን በተለያዩ ሃገራት በኢትዮጲያ ኢምባሲ ውስጥ ተሰግሰገው ያሉትን የወያኔ ተላላኪዎችን ያንሱልን.

Comments are closed.