ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን!!

በህውሃት መራሹ መንግስት ዋና አቀነባባሪነት ላለፉት 27 ዓመታት አማራውን የማጥፋት ዘመቻ እንደተፈጸመ የሚታወቅ ነው። አሁንም እነሆ የለውጥና የመደመር ዘመን ተብሎ በሚነዛበት ዲስኩር የአማራው ግድያ፣ መፈናቀልና መሰደድ መልኩን እየቀያየረ ይበልጥ እየከፋ የቀጠለ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተገደለ ፣ እየተሰደደ ፣ አጠቃላይ የአማራን ህዝብ ህብረተሰባዊ ሰላም መንሳት የሚለው የህውሃት ማኒፌስቶ ተጠናክሮ ቀጠሏል። ከላይ የተጠቀሱትን የህውሃት እኩይ ድርጊቶች በመቃወም ማክሰኞ February 19.2019 እ.ኤ.አ ከ13:00 ሰዓት ጀምሮ በፍራንክፈርት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል።

እርስዋም በዚህ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አረመኔያዊ ድርጊት ለዓለም ለማሳወቅ በዕለቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን !

የመሰብሰቢያ ቦታ ፍራንክፎርት ከኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ፊት ለፊት!

አዘጋጅ፦የአማራ ተወላጆች በጀርመን!

Recommended For You

About the Author: admin