የተሰረዘው በሳቦታጅ የተደናቀፈው እና የተጠለፈው የዶክተር አብይ አቀባበል ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን::

የተሰረዘው በሳቦታጅ የተደናቀፈው እና የተጠለፈው የዶክተር አብይ አቀባበል ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን

30.10.2018 የዶክተር አብይ አቀባበል ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን

መጀመሪያ በጣም ቀድሞ የተዘጋጀው የበርሊን 30.10.2018 የዶ/ር አብይ አቀባበል ሰላማዊ ሰልፍ በዛ አካባቢ በእለቱ ከተመዘገቡት ሰልፎች ለአምስት መቶ ተሳታፊ ፈቃድ ያገኘ ትልቁ እና ዋነኛው ዝግጅት በአካባቢው ነበረ።
የአቀባበሉም አካሄድ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለውን ለውጥ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላም በመደገፍ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በጀርመን በጉዞዋቸው የመጀመሪያ ከተማ በሆነችው በርሊንእንኳን ደህና መጡ
ለማለት እንዲሁም ለውጡን ለማበረታታት እና ለመደገፍ ነበር።

ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሰናክሎች

1.የማሳሳቻ መረጃ በማስተላለፍ በአቀባበል ሰልፉ ላይ ሊገኙ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ግራ በማጋባት
ለምሳሌ
ሀ.የአቀባበል ሰላማዊ ሰልፉን ፖስተር በመለወጥ
ለ.የአቀባበል ሰላማዊ ሰልፉን ሰአት በመለወጥ
ሐ.የአቀባበል ሰላማዊ ሰልፉንሰልፉን ቦታ አድራሻ በመለወጥ

2.ሰልፉን ለፖለቲካ አላማቸው ማስፈጸሚያ የሚያደርጉ ድርጅቶችን በሰልፉ ላይ በመጋበዝ።

3.የዝግጅቱ ሲቀርብ በመጀመሪያ የተመዘገበውን እና ፈቃድ ያገኘውን የዶክተር አብይ አቀባበል ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ሰልፉ ያልተመዘገበ ነው ፈቃድ የለውም ፖሊስ ጋ ጠይቀን ሊያረጋግጡልን አልቻሉም በሚል የማሳሳቻ መረጃ በማስተላለፍ።

4.በላዩ ላይ ደርቦ ሌላ ሰልፍ በመጥራት።

የበርሊን ዋናው ሰልፍ እንዲከሽፍ ተደርጎ በምትኩ የተደረገው ሰልፍ ላይ የነበረው ሁኔታ ታይቷል።

በዚህ አይነት ለዶክተር አብይ በበርሊን ተዘጋጅቶ የነበረውን ፍቅር እና ሰላም የተሞላበት የማንም ፖለቲካ ድርጅት ማስታወቂያ የማይሰራበት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ አዲሱን የኢትዮጵያን የለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያውያን እንኳን ደህና መጡ ብለው የሚቀበሉበትን የአቀባበል ሰልፍ ስነስርዓት ስውር እና ግልጽ በሆነ የተቀነባበረ ዘመቻ እንዲከሽፍ በመደረጉ አዘጋጆችም በሰልፉ አላማውን የሳተ አካሄድ መጠቀሚያ መሳሪያ ላለመሆን ዝግጅቱም በይዘቱ የድርጅት የፖለቲካ አላማ ማስፈጸሚያ እና ማስታወቂያ መስሪያ ስላልሆነ የዘጋጁትን ፈቃድ ያገኙበትን የዶ/ር አብይ በበርሊንአቀባበል ሰልፍ በ 30.10.2018 እያዘኑ ሰርዘዉታል።

የበርሊን ዋናው ትልቁ እንዲሰናከል የተደረገው የአቀባበል ሰልፍ ከተሰረዘ በሁዋላ በእለቱ የነበረውን ሁኔታ በምትኩ የተደረገው ሰልፍ ላይ የነበረው ሁኔታ ታይቷል።

Recommended For You

About the Author: admin