ይህንን ፎቶ ያስታዉሳሉ ?

ቀኑ ማርች 11-2007 ነበር::  የወያኔ ኮንስሌት  ኢትዮዽያ ዉስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የምትፈልጉ
ስብሰባ አንድትመጡ ብሎ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ በደብዳቤ ጠራ።
በዚይን ጊዜ በ ፍራንክፉርት የሚገኙ የ ተቃዋሚ ሃይሎች ጉዳዩን ሰምተዉ በፍጥትነት ተሰብስበው የወያኔን ደባ ለመጋፈጥ ወደ ዩገንድ ሀርበርገ (Jugend Herberge) ሄድን። አዚያም አንደደርስን ኣንዳንድ ሆዳሞች ስብሰባ ሲገቡ እኛም እዚያዉ ገብተን እንጠይቅ ብለን ልንገባ ሰንል የ ኮንስሌት ባለስልጣኑ አናንተ ተቃዋሚዎች ኣትገቡም ብሎ መከልከል ጀመረ። በዚህ ጊዜ ኣንዱ ጀግና ከመሀከላችን ይዞ በመጣዉ እንቁላል ወርዉሮ ግንባሩ ላይ ኣፈረጠው። ወዲያዉም ፎቶ ተነሳ:: ኣካባቢው ተበጠበጠ:: ሰብሰባውም ተበተነ። ፓሊስ ልጁ ሌላ መሳርያ እንዳልያዘ ፈትሾ ወዲያዉ ለቀቀዉ::  የፍራንክፈርቱ ኮንስሌት ሀላፊ የዚህ ድህረ ገፅ አዘጋጅ ፎቶዬን አንስቶ በኢንተርኔት አዉጥቶ አዋረደኝ ብሎ ክስ አቅርቦ ነበር ፍርድ ቤቱ ግን ክሱን ዉድቅ አድርጎታል:: የዛሬ 11 አመት በፊት ይህ ከመቅፅበት የተነሳዉ ፎቶ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የአመቱ ምርጥ ፎቶ ተብሎ ነበር::   በነገራችን ላይ ወያኔን ለመጣል የተጀመረው የተጀመረዉ እንቅስቃሴ ከብዙ አመታት በፊት ነበር :: ለዚህም በጀርመን የሚገኙት ኢትዮጵያዉያን ቀዳሚዉን ቦታ ይይዛሉ:: አሁንም የወያኔን አጀንዳ ይዘዉ የሚያራግቡትን ሁሉ በጥብቅ እንቃወማለን!!

Recommended For You

About the Author: admin