አቶ ምሥጢረ ኃይለ ሥላሴ ከ35  ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ገባ!

የቅንጅቱ  ምሥጢረ ኃይለ ሥላሴ (አንድነት) ከ35 ዓመታት በኋላ የሀገሩን መሬት ሊረግጥ ነው። ምሥጢረ በቅንጅት ዘመን የቅንጅት ስዊዘርላንድ የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቤ የነበረና ለሀገራችን ና ለሕዝባችን መብት በመከራከር በአውሮፓ አደባባዮቸ ማለትም ጄኒቫ/ሰዊዘርላንድ፣ ስትራስቡርግ/ፈረንሣይ፣ ብራስልስ /ቤልጅየም፣ ዌስባደን/ጀርመንና ሎንዶን/እግንሊዝ  በተለያዩ ጊዚያቶች እየተገኘ ለኢትዮጵያ ሕዝብና በስደትም ለሚጎሳቆሉ ወገኖቹ መብት ከሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቹ ጋር በመሆን ያስተባብር እንደነበር አይዘነጋም።

በተለይም ከአውሮፓ የቅንጅት የድጋፍ ድርጅቶች በተጨማሪ፣ የአፍሪካና አውስትራልያ  የድጋፍ ድርጅቶች  ሊቀ መንበር ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ከፍ ባለ ትጋትና ብቃት በመምራት የቅንጅት መሪዎች እስከተፈቱበት ጊዜ ድረስና በኋላም  የቅንጅት የከፍተኛ ልኡካን አውሮፓን በጎበኙበት ወቅት ከአውሮፓ፡ በጄኔቫ  የተባበሩት መንግሥታትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የተሳካ ግንኙነት እንዲኖር በማድረግ በኩለ መሪ ሚና እንደነበረው ይታወሳል።  አቶ ምሥጢረ በሚኖርበት ስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መስራች ከመሆኑም በላይ በሌሎች ሀገራት እንደታየው አይነት መከፋፈል ሳይኖር በመላው ስዊዘርላንድ ሁሉም አማኝ በአንድነት ተገልጋይ የሆነበት ድንቅ መንገድ ከቀየሱት መካከል አንዱ ነው።ምሥጢረ (አንድነት) በብዙዎቻችን ዘንድ በይበልጥ የሚታወቀው የቅንጅት ስዊዘርላንድ የፓል ቶክ መወያያ መድረክ ባለቤትና አስተዳዳሪነቱ ነው፡፡በዚህ ተወዳጅ የመወያያ መድረክ ከ 11 ዓመታት ጀምሮ በርካታ ታዋቂ ኢትዮጵያውያንን ቃለ መጠይቅ እያደረገ ይገኛል። በሚዛናዊነቱ የሚታወቀው ይኽ የውይይት መድረክ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የተቃዋሚ /ተፎካካሪ ድርጅቶች መሪዎችን፣ ሊቃውንትንና የጥበብ ሰዎችን በማሳተፍ ይታወቃል። ምሥጢረ የአራት ወንድ ልጆች አባት ሲሆን የመጀመርያ ልጁ ያሬድ ኃይለ ሥላሴ ከዝነኛው የዙሪክ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካ ሣይንስና በታሪክ በከፍተኛ ክብር የማስተርስ ባለዲግሪ ምሩቅ ሲሆን የ19 ዓመቱ ማረን ኃይለ ሥላሴ በፕሮፌሽናልነት የታዋቂው ኤፍሴ ዙሪክ የፕሪሜር ሊግ የእግር ኳስ ተጨዋችና የስዊሰ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ተጨዋች ነው። የ16 ዓመቱ ቅዱስ ኃይለ ሥላሴ የኤፍሴ ዙሪክ ከ 18 በታችና የስዊስ ከ17 በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጨዋች ነው። ቅዱስ በየዓመቱ በአውሮፓ የኢትዮጵያውያነ የስፖርትና ባሕል ፌደሬሸን ውድድሮች ላይ ከ6 ዓመቱ ጀምሮ ኮከብ ተጨዋች እየሆነ በተደጋጋሚ የተመረጠ በመሆኑ ብዙዎች የአውሮፓ ፌስቲቫል ታዳሚዎች ያስታውሱታል፡ ምሥጢረ በማሕበራዊ ተሳትፎዎቹ ሁሉ ከጎኑ ከማትለየው ውድ ባለቤቱ  ማክዳ በቀለ ጋር በወርሃ ጳጉሜን 2010 የውድ ሀገራቸው ኢትዮጵያን አፈር ለመርገጥ በመታደላቸው እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። 

FOTO ከግራ ወደቀኝ ምሥጢረ፣ ቅዱስ፣ ማረን፣ ማክዳና ቃለአብ ኃይለ ሥላሴ::

Recommended For You

About the Author: admin