ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ::

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጀነራል ኮንሱል በፍራንክፈርት በኢ- ሜይል

28.11.2018

ጤና ይስጥልኝ ክቡር አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ

ጉዳዩ

1.በጀርመን ሃገር ኢትዮጵያውያንን የሚከፋፍል ሰላም የሚያደፈርስ ሙስናን የሚያጎለብት አካሄድ እንድታቆሙ።

ይህ ከድሮ ያልተለወጠ አካሄድ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚከፋፍል ሲሆን ባለን የዴሞክራሲ ግንዛቤ እንዲሁም መብት ዜጎች ራሳቸውን ያደራጃሉ እንጂ በቀረ ኮሙኒስታዊ ጥርነፋ በመንግስት አይደራጁም።

የጀርመን ህግም ቢሆን በጀርመን ሃገር ነዋሪ የሆኑ የማንኛቸውንም ዜጎች የሰላም ዋስትና ያረጋገጠ ሲሆን በማንኛውም ሃይል የህብረተሰቡን ጸጥታ የሚያደፈርስ እንቅስቃሴ በህግ ክልክል ነው። ማንኛውም የዲፕሎማቲክ ጽ ቤት ውይንም ዲፕሎማት በጀርመን ሃገር ውስጥ የማንኛውንም ዜጋ መብት የሚነካ የሚከፋፍል ወደ ቅራኔ የሚመራ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድለትም።

2.በፍራንክፈርቱ ኤምባሲ የሃገር ሃብት ማባከን እና ሙስና የአካሄድ እንዲቆም።

አስቸኳይ አለም አቀፍ እርዳታ የሚያስፈጋቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር 7.8 ሚሊዮን ሲሆን በግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ 2.2 ሚሊዮን ናቸው።

የተጠየቀው ዕርዳታ 1.494 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የ478 ሚሊዮን ዶላር የበጀት እጥረት አለ። Source: UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፍራንክፈርት ስላደረጉት ስብሰባ ዝግጅት በኤአምባሲው የተሰሩት ስህተቶችን በመደበቅ በግልጽ አምኖ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይቅርታ በመጠየቅ ያላችሁን ቀጣይ መልክት ማስተላለፍ ስትችሉ በጣም እንከን የሌለበት ዝግጅት ነበር በማለት ብዙሃኑ ተካፋዮች ማእቀብ አድረገው ያልተገኙ ቢሆንም የውጭ ምንዛሪ በማባከን የምስክር ወረቅት በማሳተም እንዲሁም የምግብ እና መጠጥ ድግስ ጠርቶ በፍጻሜው የዶክተር አብይን የአንድ ዶላር በቀን እርዳታ አትርሱ በማለት ለተገኙት ሶስት እና አራት ጠርሙስ የጆኒ ዎከር ብላክ ሌብል ውስኪ ይዘው ሲሄዱ ተሰናብታችኋል።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፍራንክፈርት ስህተቱን ለመሸፈን በግለሰብ 3-4 ጠርሙስ ውስኪ ሂሳብ በጠቅላላው 60 እስከ 80 ኦይሮ ወጭ የሚያባክን ከሆነ በምን ሞራል ነው አንድ ዶላር በቀን የሚሰብከው?

ባለንበት ጀርመን ሃገር በነጻ ወይንም በጣም ባነሰ ወጭ ከቴለፎን ኮንፈረንስ እስከ ቪዲዮ ኮንፈረንስ የማድረግ አቅም እያለን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አባሎች በየቦታው ከደሞዛቸው በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ በዉሎ አበል እና በውድ ሆቴሎች በሽርሽር ሲያወድሙ ዝም ብሎ መመልከት ሙስናን መደገፍ ሲሆን የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ የሚያቃውስ ሃላፊነት የጎደለው አሰራር መቀበል ለህሊና የሚከብድ እና ማንም ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ አሁን ሃገሪቱ ባለችበት ችግር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሚስማማ አይኖርም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ለሃገራችን የተቃና ስራ እንዲሰራ እርዱኝ ባሉት መሰረት የሃገር ሃብት ሲጠፋ መመልከት ይህን ቀና ሃገር አዳኝ ጥሪ ከግምት አለማስገባት ሲሆን ሌላ አማራጭ እያለ አባካኝ አካሄድ መሄድ ከሙስና ተለይቶ የሚታይ አይሆንም።

ይህን በሚመለከት በሽቱትጋርት በሙኒክ እና በኑርንበርግ ልትጠሩ ያሰባችክሁትን ሙስናን መሰረት ያደረገ የሃገሪቱን ሃብት አውዳሚ በህግ የሚያስጠቅ በማኸበረሰቦች እውቅና የሌለው የሚያበጣብጥ እና ሰላም የሚያደፈርስ ስብሰባ ባስቸኳይ እንድታቆሙ።

ይህ ድርጊት የአንዲት የድሃ አፍሪካዊት ሃገር ሃብት ብክነት ወደ ጀርመን እና አለም አቀፍ ሜዲያዎች እንዲደርስ እናደርጋለን።

ይህን በየከተማው የታሰበውን ስብሰባ አንድ ቦታ በአንድ ቀን በፍራንክፈርት እንዲደረግ እና እኛም ካሁን በፊት እንዳደረግነው በራሳችን ወጭ በፍራንክፈርት በመገኘት የምትሉትን መስማት እንችላለን።

በሚቴክ ያንገሸገሸን በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፍራንክፈርት ካይናችን ስር እንዲካሄድ አንፈቅድም።

ከሰላምታ ጋር

ሥዩም ሀብተማሪያም

ጀርመን

ግልባጭ

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር

public@mfa.gov.et

ለአምባሳደር ኩማ ደመቅሳ በርሊን

kuma@aethiopische-botschaft.de

ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ

communications@pmo.gov.et

ለብዙሃን መገናኛ በኢ-ሜይል

amharic@dw.com

horn@voanews.com

ebc@ebc.et

info@ena.et

amharic.program@sbs.com.au

editor@ethsat.com

waltainformationcenter@gmail.com

mccreporter@yahoo.com

info@ecadforum.com

henocka2001@yahoo.com

info@zehabesha.com

admin@zehabesha.com

Recommended For You

About the Author: admin