Ethiopian Airlines Jet crashed.

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የኾነ ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲጓዝ ዛሬ መከስከሱ ተዘገበ። 149 መንገደኞችን ጭኖ የነበረው አውሮፕላን የተከሰከሰው ዛሬ ጠዋት 2 ሰአት ከ44 ደቂቃ ላይ መኾኑን ቢቢሲ ሰበር በእንግሊዝኛ ዘግቧል።

አደጋው መከሰቱን በቅድሚያ ያስታወቀው የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ነው። ጽ/ቤቱ ስለአደጋው ዝርዝር ጉዳዮችን ባይጠቅስም አደጋ ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ኃዘኑን ገልጧል።

«የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 በረራ ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር በነበረው አውሮፕላን በደረሰው የመከስከስ አደጋ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ የጠ/ሚር ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ኀዘኑን ይገልጻል::» በሚል ይነበባል የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የትዊተር መልእክት።

Recommended For You

About the Author: admin