Kenyan banks interested to enter Ethiopia.

#የኬንያ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚፈልጉ ተገለጸ።

#የተለያዩ የኬንያ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ ተቋማት በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
#የፋይናንስ ተቋማቱ ተወካዮች ከክቡር አምባሳደር መለስ አለም ጋር ትንትና ዛሬ ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ አሁን ባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ሰፊ የገበያ እድል በመጠቀም ቅርንጫፎቻቸውን በኢትዮጵያ በመክፈት ስራ መጀመር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። 
#ተቋማቱ በተለይም በግብርና፣ በአነስተኛና መካከለኛ የኢኮኖሚ መስኮች ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ መስራት የሚያስችላቸው በመሆኑ ለመግባት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
#Equity Bank በመጪው ሀምሌ 2019 በአዲስ አበባ ቢሮ ለመክፈት ዝግጅት ማጠናቀቁን አመልክቶ በቀጣይ ኤምባሲውና በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት መስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
#የFamily Bank ተወካዮች በበኩላቸው ባንካቸው በግብርና ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ በመሆኑ በኢትዮጵያ ቅርንጫፉን ቢከፍት ውጤታማ መሆን የሚያስችለው ሁኔታ እንዳለ መረዳታቸውን ገልጸዋል።

#የኢፍድሪ ቋሚ መልእክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር #ክቡር አምባሳደር መለስ አለም ለፋይናንስ ተቋማቱ ተወካዮች ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድል እንዳለ፣ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር በመሆኗም ሰፊ የገበያ እድል ለኢንቨስተሮች ያለ መሆኑን በመግለጽ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ኢንቨስት ማድረግ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችልና ኤምባሲውም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

Recommended For You

About the Author: admin