ቅሬታ ወይም አስተያየት !

ትላትና ፍራንክፈርት የኢትዩጵያን ባንዲራ ይዛችሁ አትገቡም ብላችሁ አጉላልታችሁናል አሸማቃችሁናል ዲሞክራት በሆነች ሀገር ሰው እንዴት መብቱን ይነጠቃል? አብዛኞቹም ስደት የመረጡት ጭቆና ሰልችቶአቸው ነው ስለዚህ ብታርፉ ጥሩ ነው አልደረስንባችሁም አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው ይህችን ባንዲራ ሰተውናል በደም የተነከረ ማንነታችን ነው የፈለጋችሁትን ውሰዱ ግን በባንዲራ እንዳትመጡብን ሌላው አስተናጋጆቹ ሁሉ የኦነግን ባንዲራ ለብሰው ዱላ ባልተናነሰ መልኩ ሲግላምጡን ቆዩ በጣም የገረመኝ ነገር ካሜራ ማኑ እኛን ባንዲራችንን መቅረፅ ተፀየፈ በኃላም እስቴዲየሙ ዉስጥ ጩኽት በረከተ የተወሰኑ ሰዎች ተናግረውት ተስተካክሎአል እኔም ኢትዮጵያን ላያት ሄጄ ኢትዮጵያን ሳላያት ተመለስኩ we need freedom. _Lamrot Melise


ትናንትና በፍራክፈርት በተደርገው የዶር አቢይ ኣቀባበል ስነስርአት ላይ ብዙ አቤቱታ አለን የሚሉ ሰዎች አየበዙ ነው። ቅሬታችሁን ወይም አስተያየታችሁን ላኩልን፥ ለሚመለከተዉ ባለስልጣን አናደርሳለን።

Recommended For You

About the Author: admin