ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ከስምምነት ተደርሷል::

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያ የሚገኘው እና አሜሪካ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተጀመረው እርቀ ሰላም ታላቅ ውሳኔ አስተላለፈ::
በአዲስ አበባው እና በውጭ ሃገር ያለው ሲኖዶስ ከብዙ ልፋት እና ሽምግልና በኋላ እርቀሰላሙ ተፈጽሟል:: በዚህም መሰረት በውጭ ሃገር ያለው ሲኖዶስ እና በሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ አንድ እንዲሆኑ ተወስኗል:: በዚህም መሰረት ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው የሚመለሱ እንዲመለሱ ከስምምነት ተደርሷል::

አቡነ ማቲያስም እንዲሁ የቢሮ ሥራዎችን እንዲያከናውኑና በፕትርክናቸው የሚቀጥሉ ሲሆን ዋናው መንበር ላይ አቡነ መርቆሪዮስ እንዲቀመጡ መወሰኑንና እርቀሰላሙም በዚሁ መንገድ መጠናቀቁን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ከኢትዮጵያ የመጡት አባቶችም ሆኑ በውጭ ያሉት አባቶች ስብሰባ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይቀጥላል:: የፊታችን ቅዳሜ ከጠዋቱ በ10 ሰዓት ላይም ዶ/ር አብይ አህመድ ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስን እና ሌሎች አባቶችን በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚያነጋግሩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመዋል::

Recommended For You

About the Author: admin

1 Comment

  1. Hey just wanted to give you a brief heads up and
    let you know a few of the images aren’t loading properly.

    I’m not sure why but I think its a linking issue. I’ve tried it in two different internet browsers
    and both show the same results.

Comments are closed.