ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በፍራንክፍርት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋር ተወያዩ!

Ethiopian Consulate General Office in Frankfurt

16 February . 2020 

Public

በጀርመን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በፍራንክፍርትና አካባቢዋ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋር ተወያዩ፤…………………………………………በጀርመን የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ከቆንስላ ጄኔራላችን ጋር በመሆን በፍራንክፈርትና በአካባቢዋ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ቅዳሜ የካቲት 07 ቀን 2020 በጽ/ቤታችን በአገራችን በሚገኙ የኢንቨስትንትና ንግድ አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ በማቅረብ አወያይተዋል። ክብርት አምባሳደሯ ተሰብሳቢውን በአገራችን ስላሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ግንዛቤ በማስጨበጥ ፣በአገራችን እየተካሄዱ ባሉ ተስፋ ሰጪ ለውጦች እንዲሁም ዜጎች አገራቸውን እንዴት ሊጠቅሙ እንደሚችሉ ከግል ተሞክሮቻቸው በማካፈል፣ ሊሰማሩ በሚችሉባቸው ዘርፎች ሰፊ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያውን በአንድነት በመረባረብ ከመቼውም ጊዜ በይበልጥ በመደጋገፍ አገራቸውን ለማልማት በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። በፍራንክፈርት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል አቶ ፈቃዱ በየነ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ ለኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ስለሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች፣ በሀገር ቤት ሊሰማሩ በሚችሉባቸው የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፎች፣ ከጽ/ቤታችን ሊያገኟቸው ስለሚችሉ ድጋፎች በፓወር ፖይንት የተደገፈ ሰፊ ገለጻ ሰጥተዋል። ሶስት በቡና እና በሆቴል ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች ተመክሮዎቻቸውን አካፍለዋል። ከቤቱም ጥያቄዎች ተነስተው ክብርት አምባሳደርና አቶ ፈቃዱ በጋራ ምላሽ ሰጥተዋል። በመጨረሻም ኢትዮጵያዊያኑ ለሀገራቸው ሊያበረክቱ የሚችሏቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፎች ቀጣይነት እንዲኖረው በማለም እንዲሁም ቆንስላ ጄኔራላችን የሚሰጠውን ድጋፍም ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ በኮሚቴ ተዋቅረው እንዲከናውኑ አምስት አባላት ያሉት የኮሚቴ ምርጫ ተከናውኗል።The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia#EthiopiaLandofOrigins

Recommended For You

About the Author: admin