የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ 170 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ 170 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ

በኢትዮጵያ በግጭቶችና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ህይወትን ለመታደግ የ170 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚሰጥ የአሜሪካ መንግስት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የገንዘብ እርዳታው ለተጎጂ ወገኖች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ፤ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፤ የህክምና ቁሳቁስ እንዲሁም ለግልና አካባያዊ ንጽህና አጠባበቅ የሚውል ነው ብሏል፡፡

በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱት ግጭቶች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ብዛት እንዲያሻቅብ ማድረጉን ነው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያስታወቀው፡፡

Recommended For You

About the Author: admin