Hilfe für Äthiopien – አርዳታ ለኢትዮጵያ!

5 May at 16:36 · 

Public

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በጥሬ ገንዘብና በአይነት እንዲሁም ወደ 4.4 ሚሊዮን ብር በላይ ከመ/ቤቱ ሰራተኞች ተሰበሰበ===============================================በብሄራዊ የኮቪድ 19 ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ስር የተቋቋመው ንኡሰ ኮሚቴ ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢፌዲሪ ሚሲዮኖችን በማስተባበር በኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወዳጆች ግምቱ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ በጥሬ ገንዘብ እና በአይነት አሰባስቧል።ድጋፉ ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓም የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ሃላፊ እና የብሄራዊ ሃብት አሰባሳቢ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የውጭ ሃብት አሰባሳቢ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሰቢ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የዳያስፖራ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በተገኙበት ለአገር ውስጥ ሚዲያ አካላት በተሰጠው መግለጫ ተገልጿል።በመገለጫው ከዳያስፖራው በጥሬ ገንዘብ 44, 837, 193 ብር እንዲሁም በአይነት 31, 403, 387 ብር፣ በውጭ አገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች እና ድርጅቶች 23, 272, 721 ብር እንዲሁም በአፍሪካ አገራት እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት በኮሮና ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን የሚውል ድጋፍ 10, 259 048 በድምሩ 109, 772, 349 መሰብሰቡ በመግለጫው ተመልክቷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤት እና በሚሲዮኖች ከሚሰሩ ዲፕሎማቶች፣ የወታደራዊ እና የትምህርት አታሼዎች እንዲሁም የኢሚግሬሽን ሰራተኞች 4, 417, 733.21 ብር ድጋፍ ማድረጋቸው በዛሬው መግለጫ ተገልጿል። ድጋፉን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለተቋቋመው የብሄራዊ የሃብት አሰባሳቢ የውጭ ሃብት አሰባሰቢ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሰቢ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ዛሬ ሚያዚየ 27 ቀን 2012 ዓም በተካሄደው ስነስርዓት ላይ በቼክ አስረክብዋል።በዛሬው መግለጫ ላይ በምስራቅ አውስትራሊያ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያደረገችውን የገንዘብ ድጋፍ በመወከል የማዕከላዊ እና የምዕራበ ጎንደር ሊቀፓፓስ እና የቅዱስ ሰኖደስ አባል ብጹዕ አቡነ ዮሃኒስ ፣አገር ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ዳያስፖራ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱላዚዝ ኢብራሂም እንዲሁም የዩኤስ ኮሊጅ ባለቤት አቶ ቶላ ገዳ ተገኝተው ለንኡስ ኮሚቴው ድጋፋቸውን በቼክ አስረክበዋል። በዛሬው መግለጫ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊየን፣ የኢትዮጵያ ወዳጀች እና ዲፕሎማቶች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመጠበቅ ለወገን እያደረጉ ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ ክቡራን ሚኒስትሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የኮሮና ቫይረስ የደቀነውን ስጋት መቋቋም የሚቻለው ሁሉም አካል በሚችለው አቅሙ ሲረዳዳ እና ሲተባበር በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ክቡራን ሚኒስትሮች ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Recommended For You

About the Author: admin