Where is G7 ?

by Miki Amhara (facebook)

አዲስ አበባ ወጣቶች ባለፈዉ ታፍሰዉ እስር ቤት ሲገቡ ዝም፤ ለገጣፎ ያን ያህል ቤት ሲፈርስ ዝም፤ አዲስ አበባ የእኛ ብቻ የሚል ቀረርቶ ሲነዛ ዝም፤ መንግስት እራሱ እጣ የወጣ ኮንዶሚኒየም ለኢትዮጵያዉን አላከፋፍልም ሲል ዝም፡፡ እና መቼ ነዉ መንግስትን መተቸት የሚጀመረዉ እና አካሄድን ለማስተካከል የሚሞከረዉ፡፡ እኛ ሳንሆን ይሄን ጥያቄ ደጋፊወቻቸዉ ሊጠይቁ ይገባል፡፡ የሆቴል ስለተከፈለልህ እና ይሄ ነዉ የማይባል ስልጣን መንግስት ስለሰጠህ (የአንድ ዩኒቨርስቲ ቦርድ አባል ስላደረገህ) አፍህን ይሄን ያህል የምትዘጋ ከሆነ በጣም ገራሚ ነገር ነዉ፡፡ ለነገሩ ባለፈዉ ጨርሸዋለዉ ማን የማን ስትራቴጅካል አጋር እንደሆነ፡፡ ቢያንስ እንኳን ደቡብ አካባቢ ለምሳሌ የጌዲዮ አካባቢ የተፈጠረዉን ሰባዊ ቀዉስ ሄዶ ማየት እና መፍትሄ ማፈላለግ አንድ ነገር ነበር፡፡ ችግር ስትኖር ተቀብረህ ትቆይ እና ረጋ ሲል ደግሞ ብቅ ብለህ ትደሰኩራለህ፡፡ሰዉ ይታዘበናል እኮ ይባላል፡፡

Recommended For You

About the Author: admin